Ethio Sport

Ethio Sport

የኢትዮ-በርሊን የእግር ኳስ ቡድን አመሰራረት

የኢትዮ–በርሊን የእግር ኳስ ቡድን በ October 2014 ከ10 በማንበልጥ የማህበሩ ዓባላት ወጣት መሳይ ሽማግሌዎች ( ወ መ ሽ ) እግር ለማፍታታት ፣ ደም ለማዘዋወር ፣ በየአስሩ ደቂቃ እያረፍን በማህበራዊ ጉዳይ ላይ በመወያየት እንደዋዛ
በ Schillerpark በየሳምንቱ እዑድ ቀጭን ልምምድ በማድረግ ተጀመረ ።

በፎቶግራፍ ማስረጃነት እንደምናስተውለው ወቅቱ ብርዳማ ስለነበረ የእጅ ጓንት ፣ ወፍራም ሹራብና ካፖርት ፣ የራስ ቅል ቆብና ኮፍያ በመድፋት ፣ የአዘቦት ልብስ ለብሰን የስፖርት ጫማ በመጫማት ነበር መጫወት የጀመርነው ።
ውሎ አድሮ ! ጊዜው ብዙ ከኢትዮዽያና ኤርትራ በስደት ወደ ጀርመን የገቡበት ጊዜ ስለነበር የኛን የኳስ ልምምድ ፣ መውተርተር የሰሙ ወጣቶች በብዛት ተቀላቀሉን ።
በዚህም ሂደት ቁጥራችን ከ4 ቡድን በለይ በሚወጣው ቁጥር እያሻቀበ መሄዱን በተረዱት
“ ወመሾች “ ምክክር ጉዳዩ ለኢትዮ– በርሊን ማህበር ቀረበ።
ማህበሩም በሰፊው ከተወያየበት በኋላ
1— አዲስ የመጡትን ወገኖቻችን እዚህ ከቆየነው ጋር ለመቀራረብ አንደሚረዳ:
2– ልጆችንና ወጣቶችን በማገናኘት በአካልና መንፈስ ከማጎልበት ባሻገር የሃገራቸውን ባህል ቋንቋና ልማድ ለማስተዋወቅና ለማጠናከር እንደሚያመች አምኖበት:
ገንዘብ ከዓባሎቹ በማሰባሰብና ከማህበሩ በመመደብ አስፈላጊ የስፖርት ቁሳቁሶችን ገዝቶ ፣ አሰልጣኝ መድቦ
ኢትዮ—በርሊን የስፖርት ክለብ ብሎ ቡድኑን በመሰየም ስራውን ተያያዘው ።

በመቀጠልም በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ዓባልነት ተመዝግበን በየዓመቱ በሚደረገው ውድድር ተሳታፊ ለመሆን በቃን ።