
Ethio-Berlin Sportklub
የኢትዮ በርሊን የእ ግር ኳስ ቡድን አመሰራረት
የኢትዮ–በረሊን የዕግር ኳስ ቡድን በoctober 2014 ከ10 በማንበልጥ የመህበሩ አባላት ወጣት መሳይ ሽማግሌዎች ( ወ.መ.ሽ ) እግር ለማፍታታት ፣ ደም ለማዘዋወር ፣ በየአስሩ ደቂቃ እያረፍን በማህበራዊ ጉዳይ ላይ በመወያየት እንደዋዛ
በ schillerpark በየሳምንቱ እዑድ ቀጭን ልምምድ በማድረግ ተጀመረ።
በፎቶግራፍ ማስረጃነት እንደምናስተውለው ወቅቱ ብርዳማ ስለነበረ የዕጅ ጓንት ፣ ወፍራም ሹራብና ካፖርት ፣ የራስ ቅል ቆብና ኮፍያ በመድፋት ፣ የአዘቦት ልብስ ለብሰን የስፖርት ጫማ በመጫማት ነበር መጫወት የጀመርነው ።
ውሎ አድሮ ! ጊዜው ብዙ ከኢትዮዽያና ኤርትራ በስደት ወደ ጀርመን የገቡበት ጊዜ ስለነበር የኛን የኳስ ልምምድ መውተርተር የሰሙ ወጣቶች በብዛት ተቀላቀሉን ።
በዚህም ሂደት ቁጥራችን ከ4 ቡድን በለይ አሻቀበ መሄዱን በተረዱት ” ወ መ ሽ “ወች ምክክር ጉዳዩ ለኢትዮ– በርሊን መህበር ቀረበ።
ከዚህ ቀጥሎ የስፖርት ክለቡን በተመለከት ከ አቶ ደረጀ መንገሻ የተዘጋጀ ዘገባ
ማህበሩን በሰፊው ከተወያየበት በኋላ
1— አዲስ የመጡትን ወገኖቻችን እዚህ ከቆየነው ጋር ለመቀራረብ አንደሚረዳ:
2– ልጆችንና ወጣቶችን በማገናኘት በአካልና መንፈስ ከማጎልበት ባሻገር የሃገራቸውን ባህል ቋንቋና ልማድ ለማስተዋወቅና ለማጠናከር እንደሚያመች አምኖበት:
አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ገዝቶ ፣ አሰልጣኝ መድቦ
የልጆችና የወጣቶች ቡድንአቋቁሞ:
ኢትዮ— በርሊን የስፖርት ክለብ ብሎ ቡድኑን በመሰየም ስራውን ተያያዘው ።
በመቀጠልም በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ዓባልነት ተመዝግበን በየዓመቱ በሚደረገው ውድድር ተሳታፊ ለመሆን በቃ ።
በሂደቱም የኢየትዮ— በርሊን የእግር ኳስ ቡድን:
2015 ፈረንክፈርት በተከናወነው የኢትዮ– አውሮፓ ስፖርት ፌስቲቫል ኢትዮ—በርሊን ቡድን ለመጀመርያ ጊዜ ተሳተፈ :
በ2016 በሙኒክ የኢትዮ–ጀርመን ካፕ ተሳትፎ
የፀባይና ሦሥተኛ በመሆን የሁለት ዋንጫ ተሸላሚ በመሆን አጠናቋል ።
በመቀጠልም በዚሁ ዓመት የልጆች የወጣቶችና የዋና ቡድኑን በመማሰለፍ ሦሥት ቡድን ይዞ ዴንሀግ / ሆላንድ ላይ በተዘጃው በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ፌስቲቫል ላይ በሁለቱ ታዳጊ ቡድኖች ሁለተኛ በመሆን ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ተካፍሏል ።
ከላይ በተጠቀሱትም ክንውኖች የማህበሩ ዓባሎች፣ ኢትዮጵያን የበርሊን ነዋሪወችና ወዳጆቻችን ደስተኛነታቸውን በመግለፅ ዕርዳታና ትብብራቸውን እስካሁን አላቋረጡብንም ።ለዚህም ምስጋናችን የላቀ ነው ።
የኢትዮ–ጀርመን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን የበለጠ ተጠናክሮና ተደራጅቶ የ2017 ቱን ዓመታዊ ስፖርት ፌስቲቫል አዘጋጅነት ለኢትዮ—በርሊን በመስጠቱ Juni 3/4 ለሀመጀመሪያ ጊዜ የሁለት ቀን ዝግጅት በማድረግ በኢትዮጵያ ስፖርት ዓለም ታሪክ ዙሪያ በጣም ታዋቂ የሆኑትን አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን የክብር ዕንግዳ አድርጎ ተጋባዥ በማድገግ ብዙ ህዝብ ያሰባሰበ እጅግ የደመቀ በዓል ተግባራዊ አድርጓል ። በዚሁ ዓመት በፌዴሬሽኑ ታሪክ እጅግ አወዛጋቢ በነበረው የ2017 የሮም የስፖርት ዝግጅት ከሌሎች በርካታ የፌዴሬሽኑ ዓባል ከሆኑ ክለቦች ጋር በመሆን በተቃውሞ የዝግጅቱ ተካፊይ ሳይሆን ቀርቷል ።
በ 2018 በሽቱጋርት/ ጀርመን ከ July 31— August 4 በተደረገደውም የአውሮፓ ስፖርት ፌስቲቫል የልጆችና ዋና ቡድኑን በማሰለፍ እንደገና የልጆቹ ቡድን የሁለተኛ ዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን የዋና ቡድኑም የተመሰገነ ተሳትፎ በማድረግ ግሩም ጨዋታ በማሳየት ተደናቂነትን አትርፏል ።
2019 ከ July 31— August 3.Zurich / Switzerland ላይ በተደረገው: በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ፌስቲቫል ላይ እንደተለመደው ሙሉ ቡድኑን በማሰለፍና ቤተሰብ ፣ ደጋፊወቹን ይዞ በመገኘት እጅግ የደመቀና የተሳካ ዝግጅት ላይ ተሳትፏል ። በተለይ ከፌስቲቫሉ አዘጋጆች ፣ ከዙሪክ ኢትዮጵያን ነዋሪወችና የፌዴሬሽኑ ዓመራሮች ጋር እየተናበቡ በቅርብ በመስራት የኢትዮ-በርሊን ስፖርት ክለብ መሪዎች “የኢትዮጵያ ቀን” በሚል መርሆ የዝግጅቱን ቦታ በኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲሸበርቅና የተለያዩ የባህልና ሙዚቃ ትርኢቶች ተፈፃሚነት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል ።
2020 May 30/31 ሀምበርግ / ጀርመን ላይ ሊካሄድ የነበረው በጀርመን የኢትዮጵያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል
እንዲሁም:
ከ July 29— August 01
Amsterdam / Holland ላይ ሊደረግ ታስቦ የነበረው ዓመታዊ በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ፌስቲቫል ሁላችንም በምናውቀው የ Covid 19 ዓለማዊ ወረርሽኝ ምክንያት ዝግጅቱ ተፈፃሚነት ሳያገኝ ቀርቷል ።

