የኢትዮበርሊን መሐበር ከኢትዮጵያ ኢንባሲጋር አበሮ ለመስራት ስምምነት ላይ ደረሱ!
መደመር በተግባር
“ግድግዳውን ንደን ድልድይ እንገንባ” በሚለው
የጠቅላይ ሚንስተራችን የደ/ር አብይ አህመድ መሪ ቃል መሰረት
እንሆ የኢትዮ በርሊን ስራ አስኬጅ ኮሚቴ እና የሴቶችና ልጆቾ ንዑሰ ኮሚቴ ተወካዮቾ በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቀደም ብሎ ከኤንባሲው በቀረበልን የግንኙነት ግብዣ መሰረት በ 29 08.2018 በ18 ሰዐት ተገኝተን የትውውቅ እንዲሁም በጣም ገንቢና ውጤታማ ውይይት አድርገናል ።
በውይይቱ ኤምባሲውን ወክለው የቀረቡት
1.አቶ አሰፋ ብስራት (ሚንስትር)
2.አቶ ከበደ በየነ ( ሚንስትር ካውንስል)
3.አቶ ቴዎድሮስ ግርማ( ሚንስተር) ካውንስል)። ሲሆኑ አላማው ኤምባሲው
አንደከዚህ ቀደሙ በልዪነት ሳይሆን ቀጣዪን ጌዜ አንዴት በመተባበርና በመደጋገፍ መሰራት እንዳለብን የተወያየንበትና የተማመንበት ሲሆን
ሰለ ኢትዮ- በርሊን ማህበር ግንዛቤ አንዲጨብጡ ለማድረግ ችለናል ግንኙነቱ በሁለታችንም በኩል የተደሰትንበት ተስፋ የሚሰጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በዶ/ር አብይ እና ቲሙ እየተደረገ ያለውን ለውጥ የሚደግፍ ለቀጣይም ግንኙነት መሰረት የሚጥል ሆኖ አግኝተነዋል።በኤምባሲው ተወካዮችም በኩል የኢትዮ – በርሊንን እንቅስቃሴ እንደሚያውቁ እንደሚያደንቁ አና አላማውንም እንደሚደግፉ በዐፅንዎት ነግረውን በዚህም ምክንያት ወደፊት ትልልቅ በኀላፊነት የሚሰሩ ስራዎችን
አብረውን ለመስራት ፍላጎት አንዳላቸው ገልፀውልን አኛም በደስታ ለመተባበር ፍቃደኛ መሆናችንን ቃላችንን ሰተናል።
በቀጣይ ከሚሰሩ ትልልቅ ስራዎች አንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ መሃመድ ወደ ጀርመን መምጣትን በተመለከተ የአውሮፖን ዲያስፖራ አግኝተው የሚያወያዬበትን ትልቅ መድረክ የማዘጋጀት ስራ አቅማችን በፈቀደ ሁሉ እንድናግዝ ብሎም መኅበሩ የፈጠራቸውን ጀርመን አቀፍ ፣አውሮፖ አቀፍ፤ ቻናሎችን በሙሉ በመጠቀም ጉዳዬን በማስተዋወቅ ትልቅ የግንኙነት መስመር እንድንከፍት በግልም ሊሰሩ የሚችሉ ማህበሮችንና ግለሰቦችን እንድንጠቁም ጠይቀውን ፈቃደኝነታችንን ገልፀናል። ሰለዚህ ይህን መልእክት የምትመለከቱ የምታነቡ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ለዚህ በጎ ሐሳብ በጉልበት በገንዘብ እና በሐሳብ ማገዝና መሳተፍ ብሎም በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ መታደም ለምትፈልጉ ሁሉ በኀላፊነት ፣በታጋሽነት፣በአርቆ አስተዋይነት ፣ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንድትተባበሩ የኢትዬ- በርሊን ማህበር ጥሪውን ያቀርባል ።
በተጓዳኝ በደ/ር አብይ አህመድ ለዲያስፖራው ጥሪ የቀረበበትን በቀን የአንድ ዶላር (Trust Fund)ጉዳይ ከኤንባሲው ለቀረበልን ጥያቄ በጉዳዪ ቀደም ብለን ያሰብንበትና አየተመካከርን እንደሆነ ገልፀን ይህንንም በበርሊን እና በአካባቢው ባሉ ከተሞች የማስተባበሩን ስራ ለመስራት እየተዘጋጀን መሆኑን አስረድተናል።ስለሆነም በዚህ አገራዊ የፍቅር የመተጋገዝ ብሎም የመደመር ህሣቤ አገራችንን እና ወገናችንን የምንረዳበት በጎ ተግባር ላይ መሳተፍ ለሚፈልግ አካል ሁሉ በግልም ሆነ በማኅበርም ለተደራጃችሁ የኢትዮ-በርሊን ማህበርን ክፍት መሆኑን እየገለፅን በነዚህ ከላይ በጠቀስናቸው ሁለት ጉዳዮች ከኢትዮ-በርሊን ኅጋዊ ማህበር ወይም ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በቀጥታ ግንኙነት እንድትፈጥሩ ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን።
አምላክ ኢትዮጵያንና ኅዝቦቿን ይባርክ!
ኢትዮ -በርሊን ማህበር