Sport ስፖርት

Ethio-Berlin Sportklub

የኢትዮ በርሊን የእ ግር ኳስ ቡድን አመሰራረት

   የኢትዮ–በረሊን የዕግር ኳስ ቡድን በoctober 2014  ከ10  በማንበልጥ የመህበሩ አባላት  ወጣት መሳይ ሽማግሌዎች ( ወ.መ.ሽ ) እግር ለማፍታታት  ፣ ደም ለማዘዋወር ፣ በየአስሩ ደቂቃ እያረፍን በማህበራዊ ጉዳይ ላይ በመወያየት እንደዋዛ 

 በ schillerpark በየሳምንቱ እዑድ ቀጭን ልምምድ በማድረግ ተጀመረ።

በፎቶግራፍ ማስረጃነት እንደምናስተውለው ወቅቱ ብርዳማ ስለነበረ የዕጅ ጓንት ፣ ወፍራም ሹራብና ካፖርት ፣ የራስ ቅል ቆብና ኮፍያ በመድፋት ፣ የአዘቦት ልብስ  ለብሰን የስፖርት ጫማ በመጫማት ነበር መጫወት የጀመርነው ።

ውሎ አድሮ !  ጊዜው ብዙ ከኢትዮዽያና ኤርትራ በስደት ወደ ጀርመን የገቡበት ጊዜ ስለነበር የኛን የኳስ ልምምድ መውተርተር የሰሙ  ወጣቶች በብዛት ተቀላቀሉን ።

በዚህም ሂደት ቁጥራችን ከ4 ቡድን በለይ አሻቀበ መሄዱን በተረዱት ” ወ መ ሽ “ወች ምክክር  ጉዳዩ   ለኢትዮ– በርሊን መህበር ቀረበ። 

2023

የኢትዮበርሊን ስፖርት ክለብ ከ27.05.2023 እስከ 28.05.2023 በሐምበርግ ከተማ በተካሄደዉ የ2023 የኢትዮ-ጀርመን ስፖርት ፌስቲቫል በአዋቂዎች እና በታዳጊ ልጆች ተሳትፎ አጥጋቢ ዉጤቶችን አስመዝግቧል።
Ethio-berlin S.C has participated in the Ethio-Germany sport festival held in Hamburg from 27.05.2023 to 28.05.2023.
The main Team and the Kids team have both shown a good and hopefull impression.
Ethio-Berlin F.C hat auf Ethio-Germany sport festival in Hamburg von 27.05.2023 bis 28.05.2023 teil genommen,und gute Leistung gebracht!

 

የኢትዮ -በርሊን እግር ኳስ ቡድን ጁላይ 1.2023 በተደረገዉ ፣ብዙ ቡድኖች በተሳተፉበት ፣ኢንተርኩልቱሬለስ ቱርኒር ላይ ተሳትፎ ጥሩ እንቅስቃሴን በማሳየት ለሩብ ፍጻሜ የደረሰ ሲሆን በታዳጊ ልጆች ግን አሸናፊ በመሆን የዋንጫ እና የሜዳልያ ተሸላሚ ሁኗል።

Ethio_Berlin S.C has been an aktive participant in the Interkulturelle Turnier held in Berlin ,Wedding on 01.07.2023.The Kids Team have won the Turnier while the main team achieved the 1/4 Final!

 

ከ26.07.2023 እስከ 29.07.2023 በአምስተርዳም የተካሄደዉ የኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌስቲቫል በአዉሮፓ በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ያለምንም ችግር በጣም ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል።

ቡድናችን ኢትዮበርሊንም በአዋቂዎች እና በታዳጊ ልጆች ተሳትፎ ጥሩ ጨዋታ በማሳየት አመርቂ ዉጤትን አስመዝግቧል።

በዚህ አጋጣሚ ቡድናችንን ለመደገፍ ከእነሙሉ ቤተሰባችሁ ወደ አምስተርዳም በመጓዝ እና ቡድኑ ባረፈበት ሆቴል አብሮ በመቆየት ብሎም በሚጫወትበት ጊዜ የሞራል ድጋፍ በማድረግ የተረባረባችሁ ፤እንዲሁም ታዳጊ ልጆቻችንን ተንከባክባችሁ ለጫወታ ያዘጋጃችሁ ሁሉ ድሉ የእናንተም ነዉና ከስፖርት ክለቡ  ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

ለወደፊትም ከዚህ የበለጠ ትብብር በማድረግ ቡድናችንን የበለጠ ዉጤታማ እንደምታደርጉት አንጠራጠርም።

 

 

ከዚህ ቀጥሎ የስፖርት ክለቡን በተመለከት ከ አቶ ደረጀ መንገሻ የተዘጋጀ ዘገባ

ማህበሩን በሰፊው ከተወያየበት  በኋላ    

1— አዲስ የመጡትን ወገኖቻችን እዚህ ከቆየነው ጋር ለመቀራረብ  አንደሚረዳ:      

2– ልጆችንና ወጣቶችን በማገናኘት  በአካልና  መንፈስ ከማጎልበት ባሻገር የሃገራቸውን ባህል ቋንቋና ልማድ ለማስተዋወቅና ለማጠናከር  እንደሚያመች  አምኖበት: 

አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ገዝቶ ፣ አሰልጣኝ መድቦ 

የልጆችና የወጣቶች ቡድንአቋቁሞ:   

ኢትዮ— በርሊን የስፖርት ክለብ ብሎ ቡድኑን በመሰየም ስራውን ተያያዘው ።

በመቀጠልም በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ዓባልነት  ተመዝግበን በየዓመቱ በሚደረገው ውድድር ተሳታፊ ለመሆን በቃ ። 

በሂደቱም የኢየትዮ— በርሊን የእግር ኳስ ቡድን: 

2015 ፈረንክፈርት በተከናወነው  የኢትዮ– አውሮፓ ስፖርት ፌስቲቫል ኢትዮ—በርሊን  ቡድን ለመጀመርያ ጊዜ ተሳተፈ : 

በ2016 በሙኒክ  የኢትዮ–ጀርመን ካፕ  ተሳትፎ

የፀባይና ሦሥተኛ በመሆን የሁለት ዋንጫ ተሸላሚ በመሆን አጠናቋል  ።

በመቀጠልም በዚሁ ዓመት የልጆች የወጣቶችና የዋና ቡድኑን በመማሰለፍ ሦሥት ቡድን ይዞ ዴንሀግ / ሆላንድ ላይ በተዘጃው በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ፌስቲቫል ላይ በሁለቱ ታዳጊ ቡድኖች ሁለተኛ በመሆን ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ተካፍሏል ።

ከላይ በተጠቀሱትም ክንውኖች የማህበሩ ዓባሎች፣ ኢትዮጵያን የበርሊን ነዋሪወችና  ወዳጆቻችን  ደስተኛነታቸውን በመግለፅ ዕርዳታና ትብብራቸውን እስካሁን አላቋረጡብንም ።ለዚህም ምስጋናችን የላቀ ነው ።

የኢትዮ–ጀርመን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን የበለጠ ተጠናክሮና ተደራጅቶ የ2017 ቱን ዓመታዊ ስፖርት ፌስቲቫል አዘጋጅነት ለኢትዮ—በርሊን በመስጠቱ Juni 3/4  ለሀመጀመሪያ ጊዜ የሁለት ቀን ዝግጅት በማድረግ በኢትዮጵያ ስፖርት ዓለም ታሪክ  ዙሪያ በጣም ታዋቂ የሆኑትን አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን የክብር ዕንግዳ አድርጎ ተጋባዥ በማድገግ  ብዙ ህዝብ ያሰባሰበ እጅግ የደመቀ በዓል ተግባራዊ አድርጓል ። በዚሁ ዓመት በፌዴሬሽኑ ታሪክ እጅግ አወዛጋቢ በነበረው የ2017 የሮም የስፖርት ዝግጅት ከሌሎች በርካታ የፌዴሬሽኑ ዓባል ከሆኑ ክለቦች ጋር በመሆን በተቃውሞ የዝግጅቱ ተካፊይ ሳይሆን ቀርቷል ። 

በ 2018 በሽቱጋርት/ ጀርመን ከ July 31— August 4  በተደረገደውም የአውሮፓ ስፖርት ፌስቲቫል የልጆችና ዋና ቡድኑን በማሰለፍ እንደገና የልጆቹ ቡድን የሁለተኛ ዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን የዋና ቡድኑም የተመሰገነ ተሳትፎ በማድረግ ግሩም  ጨዋታ በማሳየት ተደናቂነትን አትርፏል ።

2019 ከ July 31— August 3.Zurich / Switzerland ላይ በተደረገው: በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ፌስቲቫል ላይ እንደተለመደው ሙሉ ቡድኑን በማሰለፍና ቤተሰብ ፣ ደጋፊወቹን ይዞ በመገኘት እጅግ የደመቀና የተሳካ ዝግጅት ላይ ተሳትፏል ። በተለይ ከፌስቲቫሉ አዘጋጆች ፣ ከዙሪክ ኢትዮጵያን ነዋሪወችና የፌዴሬሽኑ ዓመራሮች ጋር እየተናበቡ በቅርብ በመስራት የኢትዮ-በርሊን ስፖርት ክለብ  መሪዎች “የኢትዮጵያ ቀን” በሚል መርሆ የዝግጅቱን ቦታ በኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲሸበርቅና የተለያዩ የባህልና ሙዚቃ ትርኢቶች ተፈፃሚነት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል ።

2020 May 30/31 ሀምበርግ / ጀርመን ላይ ሊካሄድ የነበረው  በጀርመን የኢትዮጵያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል

እንዲሁም:

ከ July 29— August 01

Amsterdam / Holland ላይ ሊደረግ ታስቦ የነበረው ዓመታዊ በአውሮፓ ኢትዮጵያውያን ባህልና ስፖርት ፌደሬሽን ፌስቲቫል ሁላችንም በምናውቀው የ Covid 19 ዓለማዊ ወረርሽኝ ምክንያት ዝግጅቱ ተፈፃሚነት ሳያገኝ ቀርቷል  ።