በኢትዮጵያ ኢምባሲ የዲያስፖራ ሃላፊ ከሆኑት አቶ ከበደ በየነ እና በበርሊን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች ጋር በ05.01.2019 የተደረገ ውይይት

በኢትዮጵያ ኢምባሲ የዲያስፖራ ሃላፊ ከሆኑት አቶ ከበደ በየነ እና በበርሊን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች ጋር በ05.01.2019 የተደረገ ውይይት

 

በኢትዮጲያ የተጀመረውን ለውጥ በመደገፍ የኢትዮበርሊ ማህበር ያለምንም ማሰላሰል፣ በኢትዮጲያ ህዝብ ድጋፍ የታጀበ ለውጥ ሰለነበረ፣ ማህበሩ ይህን ለውጥ  በበርሊን ከተማና አካባቢዎች ካሉት ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን በመሆን ዝግጅት አዘጋጅቶ በ 2018 በደማቅ ሆኔታ ማክበሩ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡፡ በዚሁ ቀን የኢትዮጵያና የኤርትራ ኢምባሲ ወኪሎች ተጋብዘው እንዲገኙ ተደርገዋል፡፡

በዚሁ ዝግጅት የተገኙት የኢትዮጲያ ኤንባሲ ወኪሎች፣ ከማህበሩ ጋር አብሮ ለመስራት  ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ከዚህ በፊት ጤነኛ ያልነበረውን ግንኙነት የኢትዮበርሊን ማህበር ከአባላቱ ባገኘው  ውክልና ወደፊት አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን መንገድ  መክረዋል፡፡

ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ጀርመን አገር ለስራ ጉዳይ በመጡበትም ግዜ የኢትዮበርሊን ማህበር ባጭር ግዜ ውስጥ በበርሊን ከተማ የድጋፍ ሰልፍ በማዘጋጀት አቀባበል አድርጓል፡፡ በቀጣዩም ቀን በ ፍራንከፉርት በተደረገው የአሊያንስ አሬና ስቴዲዎም ውስጥ  የአዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግር ዝግጅትን በማስተባበር የኢትዮበርሊን ማህበር ትልቅ አስተዋጾ አድርጓል፡፡

ይሁንና ፍራንከፈርት ውስጥ በተደረገው ዝግጅት ላይ የኢትዮበርሊን ማህበር ወኪሎች፣ የማህበሩ አባላት፣ አንዲሁም የለውጡን ደጋፊ የሆኑ ኢትዮጲያዊያን ከበርሊን ወደ ፍራንከፈርት ድረስ ሂደው፣ በዝግጅቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ለመሳተፍ በሄዱት ወገኖች ላይ አሻጥር በተሞላበት መንገድ ለንግልት ተዳርገዋል፡፡

በዚህ ዝግጅት ላይ መሪ የነበሩት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ከመላው አውሮፓ የመጡትን ኢትዮጲያውንና ትውልደ ኢትዮጲያንን አንገላተዋል፡፡

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ  አዘጋጅ ከነበሩት የኢትዮጲያ ኢምባሲ በርሊን አንዱ ሲሆን ለተከሰተው ችግር ማብራሪያ እንዲሰጡን ከማህበር ወኪሎቻችን ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር፡፡  በዚሁ  ጥያቄ መሰረት ኢምባሲው የዲያስፖራ ዘርፍ ሃለፊውን አቶ ከበደ በየነ በመላክ ማብራሪያውን  እንዲሰጡን ተደርጓል፡፡

እኚህም ወኪል በቦታው ከተገኙት ታዳሚዎች ለቀረበላቸው  ጥያቄዎች  መልስና ማበራሪያ ሰጠዋል፡፡ በፍራንከፈርት ለተደረገውም ስህተት ኢምባሲው ሃለፊኑቱን እንደሚወስድ ተናገረው ለደረሰውም መጉላላት ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

በዚሁ ስብሰባ ላይ ወኪሉ የተከሰቱትን ችግሮች ለወደፊት  እንዳይደገሙ  ጥንቃቄ አንደሚያደርጉና ከኢትዮበርሊን ማህበረ ጋርም ለወደፊቱ አብሮ  ለመስራት  ኢምባሲው እንደሚፈልግ አክለው ተናግረዋል፡፡

አሁን ያለውን ለውጥ ዲያስፖራው እንደራሱ ጉዳይ አድርጎ  ከጎን በመሆን ሊደግፈው እንደሚገባና ወደፊት ዲያስፖራው አገራቸን ኢትዮጲያን አንደ  ዲፕሎማት በመሆን ለሀገራችን መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ዲያስፖራውም ስላለው መብትና አገልግሎት ጨምረው ማብራሪያ ሰጠዋል፡፡ በአሁኑ ግዜ ኢምባሲው የሁሉም ኢትዮጲያውያን እንደሆነና በራቸውም ከፍት ሆኖ በቀና መንፈስ እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል፡፡